እንጀራ፣ በጋራ።
እውነተኛ እንጀራ፣ የትም ቢኖሩ።
ጋጋሪ በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ ትክክለኛ የሀገር ቤት እንጀራ በቀላሉ እንዲጋግሩ የሚያስችል ተፈጥሯዊ የፕሮባዮቲክ መፍትሔ ነው።
ተጠባባቂዎች ዝርዝር ውስጥ ይግቡበውጭ አገር እንጀራን ትክክል ማድረግ ከባድ ነው
እርሾን ማቆየት
ሕያው እርሾ ቀጣይ እንክብካቤ ይፈልጋል። አንድ ሳምንት ከተረሳ ይሞታል።
አብሲት ከሌለ ዓይን የለም
አብሲት ለእንጀራ ልስላሴውን እና ዓይኑን ይሰጣል። በውጭ አገር ብዙ ጊዜ የሚዘለለው ወሳኝ ደረጃ ነው።
የማይታመን ውጤት
የተለየ ዱቄት፣ የተለየ ውሃ፣ የተለየ አየር። ከቤት ርቆ ያው አሰራር የተለየ ውጤት ይሰጣል።
ሁለት ዱቄቶች። አንድ ትክክለኛ እንጀራ።
ጋጋሪ እርሾ (Ersho)
ከተፈጥሯዊ ዕፅዋት የተዘጋጀ የእርሾ እና ፕሮባዮቲክስ ውህድ ነው። ጤፍዎን እንደ ቤት እርሾ ያቦካል።
ጋጋሪ አብሲት (Absit)
ከተፈጥሯዊ ፋይበር እና ፕሪባዮቲክስ የተዘጋጀ ውህድ ነው። እንጀራን እንጀራ የሚያደርገው ልስላሴ እና ዓይን የሚሰጠውን ወሳኝ የአብሲት ደረጃ ይሠራል።
እያንዳንዱ ናሙና ከታተመ ደረጃ-በደረጃ መመሪያ ጋር ይላካል።
እንዴት ይሠራል
ይቀላቅሉ
ጋጋሪ እርሾን በ500 ግራም የጤፍ ዱቄት ላይ ጨምረው ከ500 ሚሊ ሊትር ውኃ ጋር በደንብ ያብኩት።
ለ36 ሰዓታት ያሳርፉ
በ200 ሚሊ ሊትር ውሃ ሸፍነው ሊጡን ለ36 ሰዓታት ወይም ከዚያ በላይ ያቆዩት።
አብሲቱን ይጨምሩ
ጋጋሪ አብሲትን ጨምረው በደንብ አዋህደው ሊጡን ለ4 ሰዓታት ያስቀምጡት።
እንጀራዎን ይጋግሩ
ከ300 ሚሊ ሊትር ውኃ ጋር በማላላት በምጣድ ወይም በመጥበሻ ላይ ይጋግሩት።
የተጠባባቂዎች ዝርዝር ውስጥ ይመዝገቡ
የመጀመሪያ ምርቶቻችንን በማዘጋጀት ላይ ነን። ኢሜይልዎን ያስቀምጡ። ጋጋሪ ሲገኝ ወዲያውኑ እናሳውቅዎታለን።